ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና (ትብብር ለሕልውና) የተሰጠ መግለጫ
ኢትዮጵያ በብልጽግና ግለሰባዊ አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ እጅ ከወደቀችበት ጊዜ ጀምሮ ዋነኛ መገለጫዋ፡ ጦርነት፣ የዘር ፍጅትና እልቂት እንዲሁም ፍፁም ድህነት ሆነዋል። ሀገሪቱ ሕግና ሥርዓት የፈረሰባት፣ ሚሊየኖች የከፋ ድህነት ውስጥ የወደቁባትና የተፈናቀሉባት፣ ለዜጎቿ የሚሆን ተስፋ የጠፋባት፣ ልዩ ልዩ መንግሥታዊ ሀገር አጥፊ ጦርነቶች የሚታወጁባት፣ አምባገነናዊ አገዛዝ የተጫነባት እና እንደሀገር ከወደቀ ሀገረ-መንግስትነት አልፋ የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባት እንዲሁም በቀጠናውና በዓለም አቀፍ ደረጃም በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚዊ እና በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ወደጠርዝ የተገፋችና ተሰሚነቷን ያጣች ሀገር ሆናለች።
አገዛዙ በተዛባ ትርክትና በፀረ-ሕዝብ መንግስታዊ መዋቅር ላይ የቆመ፣ ከምክንያትና ከእውነት፣ ከእኩልነትና ከሕዝቦች አሳታፊነት፣ ከፍትሕና ከነጻነት፣ ከሕዝብ ክብርና ከሀገር ሉዓላዊነት ጋር የተጣላ ሰላማዊና ገንቢ መንገዶችን የማይከተል ስለሆነ ሀገሪቱንና ሕዝቦቿን እየበላ ያለውን ጦርነት የመግታት፣ ዘላቂ ሰላም የማምጣት፣ የዜጎችን መብትና ነጻነት የማረጋገጥ፣ ሕግና ሥርዓትን የማስፈን፣ የሕዝቦችን መከራና ሰቆቃ እንዲሁም ድህነትንና ኋላቀርነትን የማስቆም ፍላጎትና አቅም የለውም። ይህ አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት ለውጭ ኃይላት ቅጥረኛ በመሆን የሕዝቦችን ጥቅም በመሸጥ ሀገሪቱን ተላላኪና ጥገኛ ሀገር አድርጓት ይገኛል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕልውና የሚገደን ሕዝባዊ ኃይሎች ይሄንን አገዛዝ በመገርሰስ የሁሉንም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕልውና የማስከበርና አዲስ ምዕራፍ የመክፈት ታሪካዊ ኃላፊነት ወድቆብናል። የሕዝባዊ ኃይሎች ታሪካዊ ተልዕኮና የመጀመሪያ ግብም የታወጀብንን የከፋ ጦርነት በጋራ በመከላከል፣ የሕዝቦቻችን ሕልውናና የሀገሪቱን ደኅንነት አደጋ ውስጥ የከተተውን የብልጽግና ግለሰባዊ አምባገነናዊ ሥርዓት በማስወገድ በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት በማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊያንን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲረጋገጡ የሚያስችል አዲስ የሽግግር ምዕራፍ እንዲከፈት ማድረግ ነው።
ከአገዛዙ ውድቀት በኋላ የሚከፈተው የሽግግር ምዕራፍ ዋና ዓላማም
1. የሕዝቦችን ሕልውናና የሀገርን ደኅንነት መታደግ፣ ሁሉንም ጦርነቶች ማስቆም፣ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ማረጋገጥ፣ ሰላምና ፀጥታን ማስጠበቅ፣ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስን ማረጋጋት፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ማሻሻልና የሀገሪቱን ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ቁመና ማስተካከል፤
2. ለሀገሪቱ ሰላምና ለሕዝቦች ቀጣይ ሕልውና ሲባል ሀቀኛ፣ ታማኝ፣ ሁሉንም ያካተተና ያሳተፈ ሕዝባዊና ሕገ መንግሥታዊ ውይይት (Constitutional Dialogue) በማድረግ ወሳኝ ሕዝባዊና ሀገራዊ ጥያቄዎችን በሕዝቦች ቀጥተኛ ተሳትፎ መመለስ ይሆናል።
በመሆኑም የብልጽግናን ግለሰባዊ አምባገነናዊ ዘረ-ፈጅ አገዛዝን ለማስወገድ፣ የሕዝቦቻችንን ሕልውናና ደኅንነት ለማረጋገጥ፣ አካታች የሽግግር መንግሥት እንዲመሰረት ለማድረግ ሕዝባዊ ድርጅታዊ አቅሞቻችንን አስተባብረን አዲስ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ምዕራፍ ለመክፈት እና በመካከላችን ያሉ ልዩነቶችን በሕዝቦቻችን ነጻ ፍላጎት፣ በመርህና በሕጋዊ ሥርዓት ተመስርቶ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በመስማማት ከታች ሥማችን የተዘረዘረው ሕዝባዊ ኃይሎች ማለትም፦
1. የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
2. የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ)
3. ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)
4. የኦጋዴን ሕዝብ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)
5. የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር (ኡጉጉሞ)
6. የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ (ቤህነን)
7. የጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን)
*የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለሕልውና* (በአጭሩ ሲጠቀስ፡ *ትብብር ለሕልውና* ) የተባለ የጋራ ትብብር መስርተናል።
ከብዙ ጥረትና ውጣ ውረድ በኋላ የኢትዮዽያ ሕዝብ በጉጉት ሲጠብቀው ለነበረው ለዚህ ታላቅና ወሳኝ ትብብር በመብቃታችን የተሰማን ደስታ ከፍተኛ መሆኑን እየገለጽን የሚከተሉትን ጥሪዎች በዚህ አጋጣሚ ለማስተላለፍ እንወዳለን።
1. ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን፣ ሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ድርጅቶች፦ አገዛዙ የሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሕልውና ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ ኃይል መሆኑን በመረዳት የትብብሩን ዓላማና የትግል መንገድ የምትቀበሉ ኢትዮጵያዊ ሕዝባዊ ኃይሎች፣ ሲቪክ ማህበራትና የፖለቲካ ድርጅቶች የሕልውና ትግላችን አጋር አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን።
2. ለአገዛዙ ታጣቂ ኃይሎችና አመራሮች፦* የምታገለግሉት አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የሕልውና አደጋ የጋረጠ፣ ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ሰላም፣ ፀረ-ዴሞክራሲ እና ዘረ-ፈጅ መሆኑን ተረድታችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ሕዝባችሁንና ሀገራችሁን ለማዳን የሚካሄደው ትግል አጋርና አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
3. ለጎረቤት ሀገራት፣ ለአፍሪካ ሀገራትና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ፦* በስልጣን ላይ የሚገኘው ዘረ-ፈጅ አገዛዝ ከሕዝብ የተነጠለ፣ በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን የማስፈን አቅምም ሆነ ፍላጐት የሌለው፣ በሕዝብ ትግል ከስልጣን ሊወገድም የተቃረበ የመሸበት አገዛዝ መሆኑን በመረዳት ከሕዝቦች፣ ከፍትሕና ከዴሞክራሲ ጎን እንድትቆሙ ጥሪ እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሀይሎች ለህልውና አንድነት
መስከረም 10/2019
ኢትዮጵያ
Sources ምንጮች:
1. Amhara Association of America (AAA) – Full Statement
This is the complete official text of the declaration, matching the content you provided.
🔗 Link: https://www.amharaamerica.org/statement-issued-by-the-ethiopian-peoples-forces-alliance-for-survival (amharaamerica.org in Bing)
2. Somalia Today – News Report on the Alliance Formation
This link provides a journalistic summary of the alliance and lists all seven member organizations.
🔗 Link: https://somaliatoday.so/seven-ethiopian-opposition-groups-form-anti-abiy-alliance (somaliatoday.so in Bing)
3. Kulu Media – OLA Clarification on the Emerging Alliance
This link is not the full alliance statement, but it provides important context about OLA’s position regarding the broader cooperation among Ethiopian armed groups.
🔗 Link: https://www.kulumedia.com/ola-clarifies-emerging-alliance-among-ethiopian-armed-groups (kulumedia.com in Bing)


